ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ሞት እንዳስመዘገበች የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ሞት እንዳስመዘገበች የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ሞት እንደመዘገበች የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ማክሰኞ እለት አስታውቋል። እንደ መንግስት መግለጫ ከሆነ የኩዋዙሉ-ናታል ክልል ነዋሪ የሆነ አንድ የ40 አመት ወንድ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶችን እንዲሁም ሽፍታ ካሳየ በኋላ ህይወቱ አልፏል። "በቤት ውስጥ እንዳለ ህይወቱ አልፏል፣ ውጤቱም እ.አ.አ ሰኔ 23፣ 2024 የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ እንደሆነ አረጋግጧል" ሲል መግለጫው አመልክቷል። ወረርሽኙ በግንቦት ወር የጀመረ ሲሆን እስካሁን 16 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ በላቦራቶሪ ተረጋግጧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik