የሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኒውክሌር ሀገራት ቀጥተኛ የግጭት ስጋት አሁን ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ነው አሉ
ሰርጌይ ራያብኮቭ በ10ኛው የ “ፕሪማኮቭ ሪዲንግስ” ዓለም አቀፍ የውጭ ግኑኝነት እና ኢኮኖሚ ባለሙያዎች መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር "ዛሬ የኑክሌር ሀገራትን ጨምሮ ቀጥተኛ የሆነ የጦርነት አደጋ ከፍተኛ ነው ወደሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል" ብለዋል።
ይሁን እንጂ ሩሲያ በኒውክሌር መከላከል መስክ የጣለችው መሰረት ደህንነቷን ለሚቀጥሉት አሥርተ ዓመታት ያረጋገጠ ነው ሲሉ አክለዋል።
"ፕሬዝዳንቱ ደጋግመው እንደተናገሩት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዋነኛነት በኒውክሌር ቅድሚያ መከላከል መስክ መሰረቶች ተጥለዋል፤ ይህም ለሚመጡት አሥርት ዓመታት ለደህንነታችን ዋስትና ነው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia