"የአሳንጅ መፈታት በአሜሪካ ምንም ነገር አይቀይርም" ስትል የስፑትኒክ የበላይ የመገናኛ ብዙሃን ቡድን ሮሲያ ሴጎድንያ ዋና አዘጋጅ ተናገረች
የአር ቲ ጣቢያ ዳይሬክተርም የሆነችው ማርጋሪታ ሲሞንያን "ሁሉም ነገር የፖለቲካ ጨዋታ ነው፡፡ ባይደን የተወሰኑ ድምጾችን ለማሸነፍ አስፈልጎታል፡፡ ምርጫ ባይኖር ኖሮ አይፈታም ነበር" ስትል ተናግራለች፡፡
አሳንጅን የዘመኑ ምርጥ ጋዜጠኛ ስትልም ገልጻዋለች። በተጨማሪም የዊኪሊክስ መስራቹ አር ቲ ላይ በድጋሚ እንዲቀርብ እንደምትፈለግ ገልፃ መጽሐፍ እንዲጽፍ ሀሳብ አቅርባለች።
"ነቃ ወዳለ ህይወቱ እንደሚመለስ ተስፋ አደርጋለሁ፣ ስርጭታችን ላይ ተመልሶ እንደሚመጣም ተስፋ አደርጋለሁ። ካስታወሳቹ ይህ ሁሉ ነገር ከመሆኑ በፊት በ2012፣ ከ12 ዓመት በፊት አር ቲ ላይ ግሩም እና ጥልቅ ፕሮግራም ያዘጋጅ ነበር፡፡ እናም በድጋሚ ወደ አየር ብንመልሰው ደስተኞች ነን" ብላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia