የፓርላማ ህንፃ ውስጥ ወረራ ስለተካሄደበት የኬንያ የተቃውሞ ሰልፍ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች፡-
🟠 የታችኛው ምክር ቤት የበጀት ረቂቅ አዋጁን ማፅደቁን ተከትሎ ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማው በመግባት ህንጻው ውስጥ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል፣
🟠 ማክሰኞ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በትንሹ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ 50 ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፣
🟠 እንደ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ያባት በኩል እህት ኦማ ኦባማ በፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ጉዳት ደርሶባታል፣
🟠 ፕሬዝዳንት ሩቶ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ሰዎች የተሰበሰቡበት የናይሮቢ የቢዝነስ ማእከል በፖሊስ ተከቦ እንደነበር ተሰምቷል፣
🟠 በመዲናዋ መኸል የተኩስ ድምፅ እና ፍንዳታ ተሰምቷል። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እና የጎማ ጥይቶችን ተጠቅሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia