የምዕራቡ ዓለም በሩሲያ የወታደራዊና ሥነ ልቦናዊ የበላይነት እንደተወሰደበት የስሎቫክ ምክትል አፈ-ጉባኤ ተናገሩ
“እውነቱን አንሽሽ፡- ምዕራባውያን ከሩሲያ ጋር የገቡትን ጦርነት እየተሸነፉ ነው። በወታደራዊ፣ በፖለቲካ እና ሥነ ልቦና፡፡ ምንም የተለየ ነገር ማድረግ አያስፈልግም፣ ፋንዲሻቹን ይዛችሁ ጠብ ጫሪዎቹ ምእራባውያን ሲሸነፉ፣ ህዝባቸው ሲያምፅባቸው እና አዲሱ ቅኝ አገዛዝ በመጨረሻም ሲወድቅ መመልከት ነው” ሲሉ የገዥው ስመር ፓርቲ አባል እና የስሎቫክ ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሉቦስ ብላሃ በቴሌግራም ቻነላቸው ተናግረዋል።
ስሎቫኪያ ከትክክለኛው የታሪክ ጎን ቆማለች ያሉት ምክትል አፈ-ጉባኤው ከሰላም፣ ከአርበኝነት እና ከማህበራዊ ፍትህ ጎን ትሰለፋለች ሲሉ አክለዋል።
ምእራባውያን ሩሲያ ላይ ጥላቻ በማስፋፋታቸው ፍርድ ይጠብቃቸዋል ያሉት ብላሃ የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የማእከል ፓርቲ ከአስቸኳይ ምርጫ በፊት በተቃዋሚዎች እየተመራ እንደሆነ እና ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን እየመሩ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
"ምዕራቡ ዓለም ከባድ ቀውስ ውስጥ ነው፡፡ ዩክሬናውያን ክራይሚያ ውስጥ ሴቶችን እና ህጻናትን በምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች በቦምብ እየደበደቡ ነው፡፡ ሙያዊ ቃላቶች ግድያ ብለው ይጠሩታል" ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia