ሩሲያ የሴቫስቶፖሉን ጥቃትን በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሐምሌ ወር ስብሰባ እንደምታነሳ የሩሲያ የተመድ ልዑክ ተናገሩ
"በየወሩ በዩክሬን ዙርያ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል፤ በሐምሌ ወርም በእርግጠኝነት ስለሚቀጥል የሴቫስቶፖሉ ጥቃት ይነሳል ብለን እናስባለን” ሲሉ ለተባበሩት መንግሥታት ጋዜጠኞች የተናገሩት ቫሲሊ ንቤንዝያ “እየሆነ ስላለው ነገር ከመናገር ወደ ኋላ አንልም” ብለዋል።
የሩሲያው አምባሳደር የተባበሩት መንግሥታት የዩክሬን ወንጀሎችን ባለማንሳት እና በበቂ ሁኔታ ባለመውቀስ ድርብ መስፈረት እየተከተለ እንደሆነ አስምረዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያን ያወገዘባቸውን በርካታ ምሳሌዎች ዘርዝረው ነገር ግን ዩክሬን በሩሲያውያን ላይ ለምትሰነዘረው ጥቃት በቂ ፀፀት እንደማያሳይ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ዩክሬን በሴቫስቶፖል ላይ በፈጸመችው አደገኛ የሽብር ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዳለ ከጥርጣሬ በላይ ነው ብለዋል።
"በዚህ ወንጀል ዩናይትድ ስቴትስ በቀጥታ መሳተፏ ምንም ጥርጥር የለውም" ሲሉ ንቤንዚያ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia