"አፍሪካ እንደ ቡድን እየደነደነችበት ባለችበት አስደሳች ጂኦፖለቲካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን" ሲሉ አንድ ባለሙያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ
"በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ትብብራቸውን ለማብዛት እየጣሩ ነው። ከብሪክስ ሀገራት ጋር ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሀገራት እርስ በርስ ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ ጥረት ሲያደርጉም ይታያል" ሲሉ ቺዶ ሙታንጋዱራ-የስዋ ተናግረዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ከፍተኛ ባልደረባው አክለውም የአፍሪካ ሀገራት ለአህጉሪቱ የገንዘብ አቋም የበለጠ ዘላቂ መፍትሄዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ ብለዋል።
"ከአሜሪካ ዶላር ጋር ተያይዞ ያለው ፈተና የአፍሪካ ሀገራትን በመገበያያው ተንሳፋፊ ተፈጥሮ ላይ እንዲወድቁ ማድረጉ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia