#አጫጭርዜናዎች
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ ሰኔ 17 የምሽት ትኩስ ዜናዎችን ይከታተሉ፡-
🟠 በሴቫስቶፖል በደረሰው የሽብር ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ተሳትፎ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሰኞ እለት ገለፁ፣
🟠 ዩክሬን በሴቫስቶፖል ባደረሰችው ጥቃት ሆስፒታል ከገቡት 28 ህጻናት መካከል ሁለቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳሉ እና ስድስቱ የድንገተኛ ህክምና ክፍል እንደሚገኙ የሩሲያ የህጻናት መብት ኮሚሽነር ማሪያ ሎቮቫ-ቤሎቫ ተናግረዋል፣
🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኪዬቭ በሴቫስቶፖል ካደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት ጋር በተያያዘ በሩሲያ የአሜሪካ አምባሳደር ሊን ትሬሲን ጠርቶ አቤቱታ ማቅረቡን አስታውቋል፣
🟠 በሩሲያ ዳግስታን ሪፐብሊክ በጠመንጃ በተፈፀመ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱን የክልሉ ጤና ሚኒስቴር ኃላፊ አስታወቁ። እሁድ እለት በደርቤንት እና ማካችካላ ከተሞች ታጣቂዎች በከፈቱት ተከታታይ ጥቃት ቢያንስ 46 ሰዎች ቆስለዋል።
🟠 የአውሮፓ ህብረት ሞስኮ ላይ ለጣለው ማእቀብ ምላሽ ሩሲያ በአውሮፓ ባለስልጣናት ላይ የምትጥለውን የጉዞ ገደብ ዝርዝር እንደምታሰፋ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፣
🟠 የአውሮፓ ህብረት የሃንጋሪን ድምፅ ችላ በማለት ከተወረሱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ወደ ዩክሬን ለመላክ መወሰኑ አሳፋሪ የቀይ መስመር ጥሰት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፒተር ሺጃርቶ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia