የኒዠር ባለስልጣናት ወደ ቤኒን የሚሄደውን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ምርመራ መጀመሩን የኒጄር ቻናል ቴሌ ሳሄል ዘግቧል።
እ.አ.አ ከሰኔ 16 እስከ 17 ምሽት ወደ ቤኒን የሚወስደው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር የተወሰነ ክፍል በመቆረጡ 370 ሜትሮች ማስተላለፊያ ትቦ ላይ ጉዳት ደረሶ የነዳጅ ዘይት እንዲፈስ ሆኗል ተብሏል።
የኒጀር የዚንደር ክልል ገዥ ኮሎኔል ኢሱፉ ላቦ “ወንጀለኞች በተባሉት ሰዎች ላይ መረጃ እና ማስረጃ ሰብስበናል እናም በወንጀሉ የተሳተፉ ሁሉም ሰዎች እንደ ወንጀላቸው በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ቅጣት ይቀጣሉ”ብለዋል።
እ.ኤ.አ ሰኔ 17፣ በሰኔ ወር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱት እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት የኒጀር የቀድሞ ፕሬዝዳንት መሀመድ ባዙም እንዲፈቱ የሚታገለው የአርበኞች ነፃ አውጪ ግንባር (ኤፍ.ኤል.ፒ.) በቧንቧ መስመር ላይ ለደረሰው ጥቃት ሃላፊነቱን ወስዷል።
መፈንቅለ መንግስቱ ከተፈፀመ ብዙም ሳይቆይ፤የኒጀር አዲስ ወታደራዊ ባለስልጣናት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቱን የተካሄደው "በጸጥታ ሁኔታ መበላሸት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አስተዳደር መጓደል" ምክንያት መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia