የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለሱዳን የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚሆን 5 ሚሊዮን ዶላር ሰጠች።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለሱዳን የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚሆን 5 ሚሊዮን ዶላር ሰጠች። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ስምምነቱን ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር ተፈራርመዋል። በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በቀጠለው ግጭት በሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለመደገፍ ያለመ ነው። የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ሴክሬታሪ ማርቲን ግሪፊዝ እንደተናገሩት " በዚህ ድጋፍ ፤በሱዳን ታይቶ በማይታወቅ ሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች የምናደርገውን የህይወት አድን ድጋፍ ማጠናከር እንችላለን" ብለዋል። በሚያዝያ ወር ለሱዳን እና ለጎረቤት ሀገራት እርዳታ ለማቅረብ በተካሄደው አለም አቀፍ የሰብአዊ ጉዳዮች ስብሰባ ላይ፣የተባበሩት አረብ ኢሚሬት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ለሱዳን 100 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል መገባታቸው ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ከተገባው ገንዘብ ውስጥ 70 በመቶው መመደቡን ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik