የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ አዲስ የጸጥታ ተልዕኮ አፀደቀ
አዲሱ ተልእኮ በያዝነው አመት በታህሳስ ወር የሚያበቃውን የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ያለውን የሽግግር ተልዕኮ(ATMIS)ይተካል።ተልእኮው የፅንፈኛው አልሸባብ ቡድን* ሃይሎች የጀመሩትን ጥቃት ለመመከት የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የሶማሊያ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ ነው።
አልሸባብ በሶማሊያ የተመሰረተ የጂሃዲስት ታጣቂ ቡድን ሲሆን ከአልቃይዳ* አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው ድርጅት ነው።በሶማሊያ መንግስት ላይ ጦር በማንሳት እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ተልእኮዎችን እያደናቀፈ ያለ ድርጀት ነው።
* አልሻባብ በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት በአሸባሪነት ተፈረጆ የታገዳ ድርጅትነው ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia