ኩባ ደቡብ አፍሪካ በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት(ICJ)በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ መቀላቀሏን የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
እ.ኤ.አ ታህሳስ 29፣ 2023 ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ስላለው ሁኔታ በጄኖሳይድ ስምምነት መሰረት በእስራኤል ላይ ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቅሬታ አቅርባ፤ ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ባለስልጣናት ላይ ጊዜያዊ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቁ ይታወሳል።
ጥር 26፣ ፍርድ ቤቱ እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከል ሁሉንም እርምጃዎች እንድትወስድ አዟል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆም አለማስገደዱን ደቡብ አፍሪካ በክሷ ጠይቃለች።
የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረሰው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ37,500 በላይ መሆኑን የክልሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia