ሩሲያ በአፍሪካ አህጉር እያሳደረች ያለው ተፅዕኖ አሜሪካንን እንዳሳሰባት አንድ የጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ ዘግቧል
እንደ ጣሊያኑ ዕለታዊ ጋዜጣ መስሳግሮ ዘገባ ከሆነ የአሜሪካ አስተዳደር ሩሲያ “ከመካከለኛው አፍሪካ፣ ከሳህል ሀገራት እስከ ሜዲትራኒያን የባህር ዳርቻ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት”ላይ እያሳደረች ያለችው ተፅዕኖ እያሳሰባት መምጣቱንገልጿል። በኒጀር፣ በማሊ እና በቡርኪናፋሶ በቅርቡ የተከሰቱት ክስተቶች እና የስልጣን ለውጦች አንጻር የሩሲያ ፌዴሬሽን ምዕራባውያንን በተለይም አሜሪካንን እና ፈረንሳይን ከአካባቢው ማስወጣት ችሏል።
ቀደም ሲል የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ በአፍሪካ ሀገራት ጣልቃ እንደማትገባ አሊያም ፈረንሳይን እንድትወጣ እንዳላደረገቻት ደጋግመው አንስተዋል።
"ማንንም አላስወጣንም። በቀላሉ የአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ከሩሲያ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፤ ከእነሱ ጋር መስራት ፈልገዋል፤ በአንዳንድ ዘርፎች ከፈረንሳይ ጋር መስራት አልፈለጉም። የእኛ ተነሳሽነት እንኳን አልነበረም። የአፍሪካ ወዳጆቻችን ተነሳሽነት ነው። በዚህ ረገድ ለምን እንደተናደዱ ግልጽ አይደለም ሲሉ የሩስያው ፕሬዝዳንት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia