በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በትላንትናው ዕለት በዋጋዱጉ ተሰብስበው "የሐሰት መረጃ እና የፕሮፓጋንዳ ስርጭትን" አውግዘዋል።
እንደሰልፈኞቹ ገለጻ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የሐሰት ዜናዎች እየተሰራጩ ሲሆን ዓላማቸውም ሞራላችንን ለማዳከም ያለም ነው ብለዋል።የቡርኪናፋሶ ዜጎች ለሀገሪቱ የፖለቲካ ሽግግር ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ሰልፈኞቹ ሊያስተላልፉ የፈለጉት "ለሁሉም የቡርኪናፋሶ ጠላቶች" በሙሉ "የኢምፔሪያሊስት ሚዲያዎች" ከሚያሰራጩት የተሳሳ መረጃ በተቃራኒ የአገሪቱ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ጥሩ መሪ መሆናቸውን ነው።
ይህ የሀሰት መረጃ እና ፕሮፓጋንዳ "የሽግግር መንግስቱን እና ሁሉንም የቡርኪናፋሶ ዜጎችን ለማዘናጋት የሚደረግ ሴራ ነው" ማለታቸውን ቡርኪና 24 ዘገባ ገልጿል።
*ፎቶዎች ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ናቸው
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia