ኒጄር የፈረንሳዩን ኦራኖ ኩባንያ ፈቃድ መንጠቋን ኩባንያው አስታውቋል።
ከኒጄሪያ ከተማ አጋዴዝ በስተሰሜን የሚገኘው የኢሞራረን የዩራኒየም ክምችት 200,000 ቶን የሚገመት ሲሆን በዓለም ላይ ካሉት ትልቁ ማዕድን ማምረቻ አንዱ ነው። ሆኖም ከአስር አመታት በላይ ምንም እንቅስቃሴ ሳይደረግበት ቆይቷል።
በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ኒያሚ ኦራኖ ኩባንያ እስከ ሰኔ 19 ድረስ ሥራውን እንደገና እንዲጀምር ካልሆነ ግን የማዕድኑን የማውጣት መብቱን እንደሚያጣ የኒጄር መንግስት አስታውቆ ነበር።
የኒጄር ማዕድን ሚኒስትር ኮሎኔል ኦስማን አባርቺ እ.አ.አ መጋቢት 19 እንዳሉት"በሶስት ወራት"ጊዜ ውስጥ "የማዕድን ማውጣት ስራውን" ካልተጀመረ መብቱን እንደሚነጠቅ እና ቦታው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል እንደሚያርጉ ማስታወቁን ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia