ሩሲያ በአንድ ሌሊት 15 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መታ መጣሏን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
"ትላንት ምሽት የኪየቭ አገዛዝ በሩሲያ ፌደሬሽን ግዛት ኢላማዎች ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራን ማክሸፉን" የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሩሲያ አየር መከላከያ ሥርዓት በደቡብ ሩሲያዋ አዲጂያ ሪፐብሊክ እና በደቡብ ምዕራብ ሩሲያ ብራያንስክ ግዛት 6 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፤ ሶስት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ደግሞ በደቡብ ሩሲያዋ ክራስናዶር ግዛት፤ ከሞስኮ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ በሮስቶቭ ግዛት አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ፤በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በምናገኘዋ ቤልጎሮድ ግዛት እንዲሁ ሌላ አንድ፤ በደቡብ ምዕራብ ሩሲያዋ ኦሪዮል ግዛት ሌላ አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ማውደማቸውን አስታወቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia