የኢትዮጵያ የብሪክስ"አዲሱ ልማት ባንክ" አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ መገኘቱን አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለፁ
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፤ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ የፖለቲካ ድጋፍ ከተለያዩ አገሮች ማገኘቷን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በሩሲያ የብሪክስ ስብሰባዎችና ተጎዳኝ መድረኮች ላይ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን ጠቅሰው ፤የብሪክስ አገራት የብሔራዊ ተወካዮችና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፎ ማድረጓን ገልጸዋል።
በመድረኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ አዳዲስ የብሪክስ አባል አገራት የብሪክስ "አዲሱ የልማት ባንክ " አባል እንዲሆኑ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ተቀምጧል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል እንደ አገር በብሪክስ ተሳትፎዋ ያላትን የጎላ ሚና ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ መቆየቷን ማብራራታቸውን ገልጸዋል።
ሩሲያ በነበረው ቆይታ ከቻይና፣ ከብራዚል፣ከደቡብ አፍሪካና ሩሲያ ጋር የተደረጉ የተናጠል ውይይቶች መደረጉን እናሀገራቱ ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባል ለመሆን ላቀረበችውን ጥያቄ ድጋፍ እንደሚሰጡ ማረጋገጣቸውን ቃልአቀባዩ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia