የሰኔ 12 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
🟠 ቭላድሚር ፑቲን እና ኪም ጆንግ ኡን በሀገራቱ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር በጋራ መመከትን ጨምሮ ፤አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።
🟠 ሲሪል ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል።
🟠 የሩስያ ፓርላማ ኮሚሽን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት እና የፌደራል ደኅንነት አገልግሎት የዩክሬን ጦር ኃይሎችን፣ የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት እና የዩክሬን ዋና የመረጃ ዳይሬክቶሬት በአሸባሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ሐሳብ አቅርቧል።
🟠 በሩሲያ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ሮሳቶም ላይ የተጣለው ማዕቀብ በኒውክሌር ደህንነት ላይ አሉታዊ ውጤት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኃላፊ ራፋኤል ግሮስሲ ተናግረዋል።
🟠 የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በዩክሬን ግጭት ዙሪያ በስዊዘርላንድ የተካሄደውን ስብሰባ ዙሪያ በመደበኛነት ግንኙነት አላቸው በሚል ከስዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሰነዘውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል።
🟠 የጀርመኑ ምክትል ቻንስለር ሮበርት ሃቤክ ሁለት ዘመዶች የናዚ ጀርመን መኮንኖች እንደነበሩ የጀርመኑ ቡንቴ መጽሔት ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia