ሩሲያ እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በአዳዲስ የኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
በሁለቱ ሀገራት መካከል በተካሄደው ስብሰባ ላይ የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ኢነርጂ ስርዓት ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት ለመተንተን እና ለማሻሻል ምክረ ሀሳቦችን ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪም ተሳታፊዎች ከዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ኤጀንሲ ጋር መተባበር ስለሚቻልባቸው መንገዶች ተነጋግረዋል።
ከውይይቱ በኋላ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐፕሊክ ልዑካን፤በዚህ አመት ከመስከረም 26 እስከ 28 በሞስኮ በሚካሄደው የሩሲያ የኢነርጂ ሳምንት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia