እስራኤል ሊባኖስን ለማጥቃት የሚያስችላትን ተግባራዊ ዕቅድ አፀደቀች

እስራኤል ሊባኖስን ለማጥቃት የሚያስችላትን ተግባራዊ ዕቅድ አፀደቀች "ማክሰኞ ዕለት የሰሜን እዝ አዛዥ ኦፊሰር ሜጀር ጀነራል ኦሪ ጎርዲን እና የኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ኦድ ባሲዩክ የስራ እቅዶችን አፅድቀው፤ በሰሜናዊ እዝ የጋራ ሁኔታዊ ግምገማ አካሂደዋል። በሁኔታዊ ግምገማው ሊባኖስን ለማጥቃት የተግባር ዕቅዶች አጽድቀው እና አረጋግጠው፤ በአውደ ግንባር ያሉ ወታደሮችን ዝግጁነት ለማሳደግ ውሳኔዎች አሳልፈዋል ”ሲል የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ተናግሯል። ከዚህም በላይ እስራኤል በሂዝቦላህ እንቅስቃሴ እና በሊባኖስ ላይ ያሉ " ህጎችን ለመለወጥ" "በጣም ተቃርባለች" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ ተናግረዋል። "በሂዝቦላህ እና በሊባኖስ ላይ ህጎችን ለመለወጥ ውሳኔ የምናስተላልፍበት ጊዜ በጣም ቀርቧል፤ በሁሉም ጦርነት ሂዝቦላህ ይደመሰሳል እና ሊባኖስ ክፉኛ ትጎዳለች"ሲል ካትዝ በ X ( በትዊተር) ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik