በኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሚመራ የልዑካን ቡድን በሩሲያ የብሪክስ አባል ሀገራት የፍትህ መድረክ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በሩሲያ ሶቺ ከተማ ትናንት መካሄድ የጀመረው ፎረም እስከ ሰኔ 14 ድረስ ይካሄዳል።
ፎረሙ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት የሚመራ ልዑክን ጨምሮ የሩሲያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሕንድ፣ ግብፅ እና የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች የሚሳተፉበት የጋራ መድረክ ነው፡፡
ፎረሙ አባል ሀገራቱ በዓለም አቀፍ ህግ መርህዎችና ደንቦች ላይ የተመሰረተ የብሪክስ ሀገራት የፍትህ ስርዓት እድገትን በተመለከተ የጋራ አመለካከት እና መግባባት ላይ ለመድረስ በማለም እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia