ዚምባብዌ ብሪክስን ለመቀላቀል ዝግጁ እንደሆነች የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር አስታወቁ
ኦፓ ሙቺንጉሪ-ካሺሪ "ዚምባብዌ [...] ለእርስ በርስ ንግድ ምቹ ከባቢ በአማራጭነተ የሚያቀርበውን የ[ብሪክስ] ተራማጅ ቡድንን ለመቀላቀል ዝግጁ ነች” ማለተቻውን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
የጋራ መከባበር፣ የጋራ እድገት እና ብልፅግና ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እድገትን ከማመቻቸት ባለፈ በገለልተኝነት እሳቤ ላይ የተገነባው የብሪክስ ሀገራት ሞዴል የርዕዮተ ዓለም ከለላዎችን ሰብሮ ማለፍ እንዳስቻለ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
“ዚምባብዌ […] ብሪክስ የምዕራባውያንን የባለአንድ ወገን ውሳኔ አሰጣጥ በመቃወም የበላይነታቸውን ያስቀራል እንዲሁም ሚዛናዊ የሆነ የዓለም ስርዓት የማሰፋፋት አቅም አለው የሚል ፅኑ እምነት አላት” ሲሉም አክዋል፡፡
ሙቺንጉሪ-ካሺሪ ብሪክስ ዓለምን ከአንድ ልዕለ ሃያላን የበላይነት ወደ ባለብዙ ወገን የዓለም ስርዓት እየመራ ነው ማለታቸውም ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia