የኔቶ ሀገራት የመከላከያ ወጪያቸውን በ18% ማሳደጋቸውን ይህም በአስርት አመታት ውስጥ ከፍተኛ ጭማሬ እንደሆነ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ተናገሩ
የኔቶ ዋና ፀሃፊ የንስ ስቶልተንበርግ "በመላው አውሮፓ እና ካናዳ የኔቶ አጋሮቻችን በዚህ ዓመት የመከላከያ ወጪያቸውን በ18% አሳድገዋል፡፡ ይህ በአስርት ዓመታት ውስጥ የታየ ከፍተኛው ጭማሬ ነው" ብለዋል።
አክለውም 23 ሀገራት 2% ወይም ከዛ በላይ የሚሆነውን አጠቃላይ ብሔራዊ ገቢያቸውን መከላከያ ላይ እንደሚያውሉ እና ይህም ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው በእጥፍ እንደሚበልጥ አክለዋል፡፡
ስቶልተንበርግ ሐምሌ 2 እና 3 ዋሽንግተን ውስጥ የሚካሄደውን የኔቴ አባል ሀገራት ጉባኤ ዝግጅት ለማስጀመር በዩናይትድ ስቴትስ ዋና ከተማ ይገኛሉ፡፡ የኔቶ አለቃ በዛሬው ዕለት ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋርም ይገናኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia