“ኢትዮጵያ ለቀጠናውና ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስትሠራ የቆየችና አሁንም ብዙ ዋጋ እየከፈለች ነው”
ይህን የተናገሩት የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ ናቸው።
በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ዓለም አቀፍ ሰላም ላይ ባተኮረ የውይይት መድረክ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለቀጠናውና ለአፍሪካ ሰላም ስትሠራ እንደቆየች ተናግረዋል፡፡
ሀገሪቱ አሁንም ብዙ ዋጋ እየከፈለች እንደሆነ በማውሳት የአፍሪካ ሀገራት የፀጥታ ችግር በገጠማቸው ግዜ ኢትዮጵያ ሁሌም ከጎናቸው እንደምትቆም አንስተዋል።
የሩሲያ መንግስት በአስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳየው አጋርነት ያመሰገኑት ሰማ ጥሩነህ ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ለሠላም ጠንቅ የሆነውን ድህነትና ኋላቀርነት ለማስወገድ የብልፅግና ፓርቲ በትኩረት እየሠራና አበረታች ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው ለዚህ የብሪክስ አባል ሀገራት በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ ሊሠሩ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia