የሩስያዋ ካዛን የብሪክስ+ ከተሞች መድረክን ታስተናግዳለች

የሩስያዋ ካዛን የብሪክስ+ ከተሞች መድረክን ታስተናግዳለች የብሪክስ+ ሀገራት የከተሞች ፎረም በሩሲያ ካዛን ከተማ ሰኔ 14 ቀን ይከፈታል። በዝግጅቱ ላይ ቻይና፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ብራዚል፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ቱርክ፣ ቤላሩስ፣ ካዛኪስታን፣ አዘርባጃን፣ ኡዝቤኪስታን፣ አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ሞሮኮ፣ ኢንዶኔዥያ እና ሜክሲኮን ጨምሮ ከ21 ሀገራት የተወጣጡ 200 የማዘጋጃ ቤት ሀላፊዎች ይሳተፋሉ። የኢትዮጵያ ከተሞች ማህበር ዋና ዳይሬክተር አንዱዋለም ጠናው ኢትዮጵያን በመወከል በመድረኩ እንደሚሳተፉ ታውቋል። ፎረሙ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማሲያዊ አካዳሚ እና የሰብዓዊ ኤጀንሲው ሮሶትሩድኒቼስትቮ ድጋፍ በካዛን ማዘጋጃ ቤት የተዘጋጀው ነው። ተሳታፊዎች የብሪክስ+ ሀገራት ከተሞች እና ማዘጋጃ ቤቶች ማህበርን ስለማቋቋም፣ መስራች ጉባኤውን ስለማካሄድ፣ መሪን ስለመምረጥ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱን ስለመወስን፣ የስራ እቅድ ስለመዘርዘር እና በጋራ ፕሮጀክቶች ላይ ስለመወያየት ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዝግጅቱ ፕሮግራም ይጠቁማል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik