የዙማ ፓርቲ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ አንድነት መንግስትን ላለመቀላቀል ወሰነ
በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሚመራው ኡምኮንቶ ዌ ሲዝዌ (ኤም.ኬ) ፓርቲ የደቡብ አፍሪካ የብሔራዊ አንድነት መንግስት ምስረታ አካል እንደማይሆን እና ፓርላማ ውስጥ ተቃዋሚዎችን እንደሚመራ የፓርቲው ቃል አቀባይ ንህላሙሎ ንድሌላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ንድሌላ ዙማን ወክለው በሰጡት መግለጫ ኤም.ኬ የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና የኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮችን ያካተተውን “ተራማጅ ኮውከስ” እንደሚቀላቀል ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
"ይህ የተባበረ ጥረት አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም የ2024ቱ ምርጫ የኢኮኖሚ ነፃነት፣ ሥር ነቀል የኢኮኖሚ ለውጥ፣ የዘር እኩልነት እና መሬት ማስመለስን የሚቃወሙ ቀኝ ዘመም እና ለውጥ የማይፈልጉ ኃይሎች እንዲጠናከሩ አድርጓል" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia