ብልጽግና ፓርቲ ከብሪክስ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንደሚመሰረት አስታወቀ

ብልጽግና ፓርቲ ከብሪክስ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንደሚመሰረት አስታወቀ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች “ብሪክስ እና አጋር ሀገሮች” ፎረም ባደረጉት ንግግር ብልጽግና ፓርቲ ከብሪክስ ቡድን ጋር ግኑኝነቱን ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ፓርቲያቸው ብሪክስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በቅርበት ሲከታተለው እንደቆየ ገልጸው ማዕቀፉ የዓለም የኢኮኖሚና ፖለቲካ ምህዳርን የመቀየር አቅም እንዳለው ተናግረዋል። የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራትና ከአሰራር ማዕቀፉ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት እየሰሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል። ብሪክስ አዲስ አባል ሀገራትን ለማካተት ለወሰደው ጠንካራ እርምጃ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አደም ፋራህ ውሳኔው ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል እንድትሆን እድል የፈጠረ እንደሆነ ገልፀዋል። “የብሪክስ አባል በመሆናችን ክብር እና ደስታ ይሰማናል፡፡ በቡድኑ ውስጥ ተሳትፏችን የተመላከተውን የጋራ እድገት እና ብልፅግና በጉጉት እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik