ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዶንዬትስክ ውስጥ በመገናኛ ብዙሃን ሰራተኛ ላይ የተፈፀመውን ግድያ እንዲያወግዙ ሩሲያ ጠየቀች
ሞስኮ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም ዩኔስኮ በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ ውስጥ በ News.ru ድረ-ገፅ ወታደራዊ ዘጋቢ ኒኪታ ሲትሳጊ ላይ የተፈፀመውን ግድያ እንዲያወግዙ ትጠይቃለች ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ እሁድ እለት ተናግረዋል።
News.ru በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ ኡግሌዳር ከተማ አቅራቢያ በዩክሬን መከላከያ ሀይሎች ጥቃት የወታደራዊ ፎቶ ዘጋቢው ሲትሳጊ መገደሉን አስታውቋል።
ጋዜጠኛው በዩክሬን ጦር ኢላማ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ዩክሬን በመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት መሰንዘሯን የገለፁት ቃል አቀባዩ ጥቃቶቹ መደጋገማቸውን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia