ኬንያዊው ወጣት በ800 ሜትር ሩጫ በታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰው ሆነ
የ19 ዓመቱ ኢማኑኤል ዋንዮኒ ባለፈው ቅዳሜ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ተካሂዶ የነበረውን የ800 ሜትሩ የሩጫ ውድድር በ1 ደቂቃ ከ41.70 ሰከንድ ሮጧል።
ከአንድ ቀን በፊት፤ በግማሽ ፍፃሜው ደካማ ውጤት አስመዝግቦ የነበር ቢሆንም ድሉን ለማስሳካት ችሏል።
"ትናንት ባልወድቅ ኖሮ ዛሬ እንደዚህ አልሮጥም ነበር፣ ስለዚህ ሁሉም ነገር በምክንያት ነው የሚሆነው" ብሏል።
በውጤቱ መሰረት ዋንዮኒ በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ችሏል። አትሌቱ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ነበር።
የ800 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በሌላኛው ኬንያዊ ዴቪድ ሩዲሻ የተያዘ ነው። ያስመዘገበው ሰዓት 1 ደቂቃ 40.91 ሰከንድ ነው። ሪከርዱ እ.አ.አ በ2012 ነው የተመዘገበው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia