ኢራቅ እና ዮርዳኖስ ከዩክሬን የሰላም ጉባኤ የጋራ መግለጫ ሰነድ ፊርማቸውን አነሱ

ኢራቅ እና ዮርዳኖስ ከዩክሬን የሰላም ጉባኤ የጋራ መግለጫ ሰነድ ፊርማቸውን አነሱ ውሳኔውን ተከትሎ ሰነዱን የደገፉ ሀገራት ቁጥር ከ91 ወደ 77 ዝቅ ማለቱን በሰነዱ መጨረሻ የተቀመጠው የፈራሚ ሀገራት ዝርዝር አሳይቷል። በስዊዘርላንድ አስተናጋጅነት በተካሄደው ኮንፈረንስ የተሳተፉ ነገር ግን መግለጫው ላይ ያልፈረሙ ሀገራት ቁጥር ከ12 ወደ 14 አድጓል። ከኢራቅ እና ዮርዳኖስ በተጨማሪ ብራዚል፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ አርሜኒያ፣ ባህሬን፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሊቢያ፣ ሜክሲኮ እና ታይላንድ ሰነዱን አልፈረሙም። ስዊዘርላንድ ሰኔ 8 እና 9 ከሉሰርን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው በርገንስቶክ ሪዞርት በዩክሬን ዙርያ ከፍተኛ ደረጃ ኮንፈረንስ አዘጋጅታለች። በርን የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ቭላድሚር ኮክሎቭ ሩሲያ የጉባዔው ግብዣ እንዳልደረሳት እና ቢድረሳትም ተሳትፎ የማታደርግ እንደነበር በሚያዝያ ወር ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik