ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሀገራቱን ህዝቦች እና መንግሥታት ግንኙነት በማሳደግ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ከፍ እንደሚደርጉ ተገለፀ
ይህን የገለፁት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ናቸው።
አደም ፋራህ ከሩሲያ ዩናይትድ ፓርቲ ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል የጽሕፈት ቤት ሃላፊ አንድሬ ክሊሞቭ ጋር ከሰኔ 9 እስከ 12 በሚካሔደው "የዓለም አብላጫ ለብዙኃን ሥርዓት" መድረክ ጎን ለጎን ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የቆየ ታሪክ ስላለው ጠንካራ የሩሲያ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አውስተዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን የሩስያ መንግስት እና ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው ለሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ትልቅ እድገት እንደሆነ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የግብርና ምርቶች እንደ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሰሊጥ እና የተለያዩ የእህል ዓይነቶችን በቀጥታ ወደ ሩሲያ ገበያ ለመላክ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑንም አስምረውበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia