የኡጋንዳ ኢኮኖሚ በመጪው የበጀት ዓመት ከ6.4% እስከ 7% የዘላቂ ዕድገት አቅም እንደሚመለስ የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር አስታወቁ
የ2024/2025 ዘመን የሀገሪቱን በጀት ያቀረቡት የፋይናንስ ሚኒስትሩ ማቲያ ካሳጃ ኢኮኖሚው በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በሁለት አሃዝ የማደግ እድል እንዳለው ተናግረዋል።
"ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ የኡጋንዳ ኢኮኖሚ ከተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ቀውሶች ሙሉ በሙሉ ማገገሙን ሪፖርት ሳደርግ ደስተኛ ነኝ። ከ2022/2023 5.3% ጋር ሲነፃፃር በ2023/2024 የበጀት ዓመት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በ6% ያድጋል" ሲሉ ሚኒስትሩ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia