ታንዛኒያ የአሜሪካ ዶላር አጠቃቀም ላይ ገደብ ጣለች
የታንዛኒያ የፋይናንስ ሚኒስትር ዶ/ር ምዊጉሉ ንቸምባ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የአሜሪካን ዶላር በሀገር ውስጥ ግብይት በስፋት ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚከለክል መመሪያ አውጥተዋል።
2006 በወጣው የታንዛኒያ ባንክ ህግ ክፍል 26 ስር በተደነገገው መሰረት ከሰኔ 24 ጀምሮ ሁሉም ግብይቶች እና ማስታወቂያዎች በታንዛኒያ ሺሊንግ መከናወን አለባቸው።
ዶ/ር ንቸምባ የዶላር አጠቃቀም የዶላር እጥረትና የታንዛኒያ ሺሊንግ ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ አሉታዊ ተፅእኖዎች እንዳሉት ጠቁመዋል። የመንግስት አካላትን ጨምሮ ተቋማት የፋይናንስ መረጋጋትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማጎልበት በመመርያው መሰረት
ደንቦቻቸውን እንዲያስተካክሉ ጠይቀዋል።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። እርምጃው ተቀማጭ የውጭ ምንዛሪን ለመቆጠብ እና የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia