የሞሮኮ ማዕድን ማውጫ ኩባንያ ማነዣም የዩናይትድ ኪንግደም ጋዝ ኩባንያ ቅርንጫፍ፤ ሳውንድ ኢነርጂ ሞሮኮ ምስራቅን፤ እንደገዛ ዘገባዎች አመለከቱ
የግብይቱ አጠቃላይ ዋጋ 45.2 ሚልየን ዶላር ነው። ሽያጩ በምስራቅ ሞሮኮ በሚገኘው ቴንድራራ ጋዝ መስክ ምርትን ለማሻሻል ወሳኝ እንደሆነ ሳውንድ ኢነርጂ ገልጿል።
በቦታው የሚመረተው ምርት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በዓመት 100 ሚልየን ኪዩቢክ ሜትር በማውጣት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ማነዣም አስታውቋል።
ኩባንያው ሞሮኮን ከስፔን ጋር ከሚያገናኘው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ጋር በማስተሳሰር ምርቱን ወደ 280 ሚልየን ኪዩቢክ ሜትር ለማሳደግ አስቧል።
የማነዣም ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢማድ ቱሚ "ቡድኑ በአፍሪካ ውስጥ ሌሎች የጋዝ ንብረቶችንም በንቃት ይፈልጋል" ማለታቸው ተጠቅሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia