ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 36% መድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁሶችን በሀገር ውስጥ እንደምታመርት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ተናገሩ
ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ ይህንን የገለፁት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ የሀገሪቱን የጤና አገልግሎት በማዘመንና በማስፋፋት በኩል በተገኘው ውጤት የእናቶች፣ ህጻናት እና ጨቅላ ህጻናት የጤና አገልግሎት መሻሻሎችን አስመዝግቧል።
የሀገሪቱን አምራች ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሆነው "ኢትዮጵያ ታምርት" ብሔራዊ እንቅስቃሴ የሀገር ውስጥ መድሐኒትና የሕክምና ግብአት ምርት በማሳደግ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን የጤና ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ ጠቁመዋል።
ባለፉት 100 ቀናት ብቻ ሁለት የፋርማሱቲካል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስራ መጀመራቸውንና መድኃኒት በማምረት ላይ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia