ለዩክሬን ግጭት ብቸኛው መፍትሄ አዲሱን የሩሲያ የሰላም ሃሳብ ተግባራዊ ግድረግ ነው ሲሉ የኢራን የፖለቲካ ተንታኝ ተናግረዋል።
ሩሆላህ ሞዳበር ሩሲያ ለዩክሬን ግጭት፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ያቀረቡት የሰላም ሃሳብ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
"ቀደም ሲል የቀረቡትን የሰላም ሃሳቦችን እና የሚንስክ ስምምነቶችን ችላ በማለት በዩክሬን ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ሊረዱ የሚችሉትን አራት ዙር ድርድሮች ችላ በማለት የምዕራቡ ዓለም ቀውሱ እንዲቀጥል አድርገዋል" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግሯል።
ባለሙያው የሰላም ሃሣቡን "ግልጽ የሆነ" ብለውታል። ከኔቶ፣ ከአሜሪካ፣ ከፈረንሣይ እና ከጀርመን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወታደራዊ እና ሁሉም ዓይነት ድጋፍ ቢደረግም ፤ የግጭቱ ሚዛን በሩሲያ እጅ ላይ ነው ብለዋል ።
ሞዳበርም ምዕራባውያን እና ኪየቭ ይህን የሰላም ስምምነት ሃሳብ ውድቅ ካደረጉ ለሚፈሰው ደም ተጠያቂ ይሆናሉ፤ በማለት ፑቲን በመግለጫቸው ካነሱት ሃሳብ ጋር ይስማማሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia