እ.ኤ.አ በጁላይ 2023 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱት የኒጀር ፕሬዝዳንት መሀመድ ባዙም ያለመከሰስ መብት በኒጀር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተነስቷል ።
ውሳኔው በቀድሞ ፕሬዝዳንት ላይ ሊከፈት ለሚችል የፍርድ ሂደት መንገድ ይከፍታል ፤መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎ ባዙም እና ባለቤታቸው ሀዲዛ በፕሬዝዳንት መኖሪያ ቤት መታሰራቸው ይታወቃል።
ባዙም በሀገር ክህደት፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ በመደገፍ እና ሀገሪቱን ለማተራመስ በማሴር በኒጀር ባለስልጣናት ተከሰዋል።
በተለይም በመፈንቅለ መንግስቱ ወቅት ወታደራዊ ድጋፍ ለማግኘት እንዲሁም ጣልቃ እንዲገቡ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በስልክ መገናኘታቸው ተነግሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia