የዩክሬን ግጭት መነሻ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ሳቢያ የተፈጠረ ችግር ሳይሆን ፤ የምዕራቡ ዓለም አደገኛ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ውጤት ነው ሲሉ ፑቲን ተናገሩ።
ኔቶ ዩክሬንን በሩሲያ ላይ የጦር ሰፈር ለማድረግ ሞክሯል፣ ህዝቦችን እርስበርስ ለማጋጨት የተቻለውን ሁሉ አድርጓል ሲሉ ፑቲን አክለዋል።
የችግሩ መዘዝ መላውን ዓለም እየጎዳ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
ሩሲያ የዩክሬንን ግጭት አልጀመረችም፤ ነፃነታቸውን ባወጁ ዜጎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ የጀመረችው ኪየቭ ነች ሲሉ ፑቲን አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia