ሁለት የእንግሊዝ ዜጎች 6.48 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የኮኬይን እፅ ከጋና ወደ እንግሊዝ ለማጓጓዝ ሞክረዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።
ሰኞ እለት የሀገሪቱ ባለስልጣናት በዋና ከተማዋ አክራ በኮቶካ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 166 ኪሎ ግራም የሚጠጋ እጽ በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ዘመቻው የተካሄደው በጋና አደንዛዥ እፅ ቁጥጥር ኮሚሽን እና በእንግሊዝ የወንጀል ቁጥጥር ኤጀንሲ የጋራ ቅንጅት ነው።
በብሪቲሽ አየር መንገድ በረራ ወደ ለንደን ጋትዊክ አውሮፕላን ማረፊያ ሊጓዙ የነበሩት ተጠርጣሪዎቹ፤ አደንዛዥ እፁን በ72 ኪሶች ውስጥ ከፋፍለው በስድስት ሻንጣዎች ውስጥ ደብቀው እንደነበር የጋና አደንዛዥ እፅ ቁጥጥር ኮሚሽን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia