ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በመጠቀም በውጭ ርዳታ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ ጥረት እያደረገችመሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ።

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በመጠቀም በውጭ ርዳታ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ ጥረት እያደረገችመሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ። ይህን ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ነው። በበጋ መስኖ በሩዝ ልማትና ሌሎች ሰብሎችም ከፍተኛ ምርት መገኘቱን ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ የተመጣጠነ አመጋገብ ሥርዓት እንዲኖረው እና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ የሌማት ትሩፋት መጀመሩን አዲስ እድል እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል። በተጨማሪም በግብርናው ዘርፍ ዜጎች የራሳቸውን የምግብ ዋስትና እንዲያረጋግጡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በርካታ መድረኮችና ምክክሮች መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል። ስፑትኒክኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik