በደቡብ አፍሪካ በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ሳቢያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አስታወቁ
"ደቡብ አፍሪካ በአጠቃላይ 5 በላቦራቶሪ የተረጋገጠ ውጤቶችን ማግኘቷን እና ምልክቱ የታየበት ህመምተኛ እ.አ.አ ሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2024 በቴምቢሳ ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉን" የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ፋህላ በመግለጫቸው አስታወቀዋል።
መግለጫው እንደተጠቀሰው በምርመራው የተገኙ ውጤቶች የሚያሳዩት ፤ ወረርሽኙ ወደ ተከሰተበት አካባቢ ያልተጓዙ እድሜያቸው ከ30-39 ክልል ውስጥ የሆኑ ወንዶች ላይ መሆኑ፤ በሽታው በየአካባቢው እየተስፋፋ መሆኑን ያመለክታል ብሏል።
ቀደም ሲል የዝንጀሮ በሽታ ተብሎ የሚጠራው ኤም ፖክስ ከዱር እንስሳት ወደ ሰዎች ሊተላለፉ የሚችል እና በቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ ነው። የተለመዱ ምልክቶቹም ትኩሳት፤ሽፍታ እና የሊምፍ ኖዶች እብጠት ናቸው። በሽታው በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በብዛት የሚከሰት ሲሆን በሽታውእ.ኤ.አ እስከ 2022 ድረስ በዓለም ዙሪያ ተሰራጭቶ ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ እስከሚደርስ ድረስ በብዛት አይታወቅም ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia