የሰኔ 6 ረፋድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች፡-
🟠 የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ሶስት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ትላንት በአንድ ሌሊት በሩሲያዋ ያሮስቪል እና ቭላድሚር ክልል ላይ መትተው መጣሉን ገለጸ።
🟠 ትላንት ምሽት በአርሜኒያ የፓርላማ ህንፃ አቅራቢያ በተነሳ ግጭት፤ ፖሊሶችን ጨምሮ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ 101 የሚደርሱ ሰዎች ፤ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል።
🟠 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በ ቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለዩክሬን የ310 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚሰጡ ፅህፈት ቤታቸው አስታውቋል።
🟠 አሜሪካዊው ኢሎን መስክ የዩክሬን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አሜሪካ በ"ጥቁር መዝገብ" በአሸባሪነት ዝርዝር እንድትመዘግባቸው እና ማዕቀብም እንዲጣልባቸው ጥሪ አቅርቧል።
🟠 በሁለተኛው የሩሲያ ስትራቴጂክ ያልሆኑ የኒውክሌር ሃይሎች ልምምድ ወቅት የኤሌክትሮኒካዊ ሚሳኤል ማስወንጨፉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia