ሴኔጋል በሳንጎማር የነዳጅ ዘይት ማምረት ከጀመረች በኋላ የነዳጅ ዘይት አመራች ሀገራት ደረጃን ተቀላቀለች
"ይህ ለሴኔጋል እና ለውድሳይድ ኩባንያ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉ በሳንጎማርን ነዳጅ የሚያወጣው የአውስትራሊያው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜግ ኦኔይል ተናግረዋል።"ይህ የሳንጎማር የነዳጅ ዘይት ትልቁ ምዕራፍ ነው።" ከእቅዳችንም የቀደመ ነው ።
ከአስር አመታት በፊት የተገኘው የሳንጎማር የነዳጅ ዘይት ጕድጓድ በቀን ወደ 100,000 በርሜል የነዳጅ ዘይት እንደሚያመረት ይጠበቃል። በየካቲት ወር ተንሳፋፊ የምርት ማከማቻ እና ጭነት (FPSO) መርከብ ግንባታ የተከናወነበት ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው ከ4.9 እስከ 5.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ነው።
ውድሳይድ ኩባንያ በፕሮጀክቱ 82 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ቀሪው 18 በመቶ የሚሆነው ደግሞ የሴኔጋል ብሄራዊ የነዳጅ ኩባንያ ፔትሮሰን ነው።
አዲስ የተመረጡት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የሀገሪቱን የነዳጅ፣ የጋዝ እና የማዕድን ዘርፎች ኦዲት ለማድረግ እና ከውጭ ኮንትራክተሮች ጋር ውል ለመፈራረም ማቀዳቸው አይዘነጋም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia