በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም ላይ እጅግ የከፋ ነው ብሎ በገለጸው የሱዳን ስደተኞች ሁኔታ፤ ግጭቱ ከጀመረበት እ.አ.አ ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ 7.26 ሚሊዮን አዲስ ተፈናቃዮች እና 2.83 ሚሊዮን ከዚህ ቀደም የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸው አስታወቋል።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አክሎም ከ2 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን አስታውቋል።
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፤በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ሲገለፁ ምናልባትም ቁጥሩ እስከ 150,000 ሊደርስ እንደሚችል ግምት አለ።እንዲሁም ዜጎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ እና በተለይ በዋና ከተማዋ ካርቱም የከፋ ውድመት እየደረሰ መሆኑ ተነግሯል።
ይህ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀለው ዜና በሱዳን ከፍተኛ የሆነ ረሃብ ያስከተለ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጦት የደረሰ እና የእርዳታ አቅርቦት ላይ እክል የፈጠረ በመሆኑ፤ አስከፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ ፈጥሯል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ አቅርቦትን የሚያደናቅፉ "ስልታዊ እንቅፋቶች" መኖሩን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia