የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጊኒ ተሬኪን ኢትዮጵያ እያካሄደች ባለችው ብሄራዊ ምክክር ዘላቂ ሰላም እንደምታረጋግጥ ያላቸውን ተስፋ ገለፁ።

የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጊኒ ተሬኪን ኢትዮጵያ እያካሄደች ባለችው ብሄራዊ ምክክር ዘላቂ ሰላም እንደምታረጋግጥ ያላቸውን ተስፋ ገለፁ። አምባሳደር ተሬኪን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ብሔራዊ ምክክር ከኢዜአ ጋር ልዩ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። አምባሳደር ተሬኪን በምክክር መድረኩ ኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይቶች አድርገው፤ ለሚነሱ ዘርፈ ብዙ ቅሬታዎች መፍትሄ ማስቀመጥ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስጠበቅ ያለውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። "በመሆኑም በውጤቱ በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በብሔራዊ ውይይቱ ላይ መሳተፍ አለባቸው።" አምባሳደሩ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ንግግር በመጥቀስ በጉልበት ምንም አይነት ድል እንደማይገኝ አስታውሰው፤ በሃይል እርምጃ አሸናፊ እና ተሸናፊ አይኖረም ፤ ምክንያቱም ተሸናፊውም ስለ በቀል ያስባል። በዚህ መንገድ ደግሞ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል። ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት እና ዘላቂ ሰላምን ማስጠበቅ የሚቻለው በውይይት ብቻ ነው ሲሉ አምባሳደር ተሬኪን ተናግረዋል። እርግጥ ነው ፤ብሄራዊ ምክክር ቀላል ሥራ አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ ቅሬታዎችን በቀላሉ መተውና እና ወደ ፊት መራመድ በጣም ከባድ ነው፤ግን በምክክር ግን ሊቻል ይችላል። ''ለዚህም ነው ብሔራዊ ምክክሩን አጥብቀን የምንደግፈው። ሩሲያ ለማገዝ ዝግጁ ነች፤የተሳካ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ምክክር ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik