የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ስለፈፀሙት ዮዲት ሱሚንዋ ቱሉካ ምን ይታወቃል?
▪ ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆኑት የ56 ዓመቷ ሴት የተወለዱት በሀገሪቱ ኮንጎ ሴንትራል ግዛት ነው።
▪ ከብራሰልሱ ፍሪ ዩኒቨርሲቲ በሠራተኛ አስተዳደር ሳይንስ እና በሰው ሀብት አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ይዘዋል።
▪ በቤልጂየም ከሚገኘው የሞንስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአፕሊድ ኢኮኖሚክስ፣ ኦፕሽን ፋይናንሺያል ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
▪ አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ብራስልስ ከሚገኘው የፕሮሞሽንና ተከታታይ ትምህርት ክፍል በአካውንቲንግ ዲግሪ አግኝተዋል።
▪ መጀመሪያ የሥራ ዓለም በባንክ ዘርፍ የሰሩ ሲሆን ወደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት፤ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ቢሮ ጭምር ሠርተዋል።
▪ እ.ኤ.አ በ2012 ቱሉካ ሱሚንዋ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የበጀት ሚኒስትር አማካሪ ሆነው ሰርተዋል።
▪ በመቀጠልም በሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት የስትራቴጂክ ክትትል ምክትል አስተባባሪ በመሆን አገልግለዋል።
▪ እ.አ.አ ከመጋቢት 24 ቀን 2023 ጀምሮ ቱሉካ ሱሚንዋ የUገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ፖሊሲ በማቀድ እና ፕሮግራም በማዘጋጀት የሀገሪቱን የፕላን ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia