ሃማስ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በባይደን የቀረበውን ስምምነት ውድቅ ማድረጉን ዘገባዎች አመላክተዋል።
የፍልስጤም ንቅናቄ ሃማስ ታጋቶችን ለማስለቀቅ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ ማድረጉን የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን የእስራኤል ባለስልጣንን ጠቅሰው ማክሰኞ ዕለት ዘግበዋል።
ባለሥልጣኑ እስራኤል ከሃማስ በአሸማጋዮች በኩል ምላሽ እንደሰጠ ገልፀው ፤ የንቅናቄ ቡድኑ የባይደን የተሱስ አቁም ዋና ማዕቀፎችን ቀይሯል ብለዋል።
ሰኞ እለት ሃማስ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ሰርጥ ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቀውን ውሳኔን በደስታ መቀበሉ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ እ.አ.አ ግንቦት 31 በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የቀረበውን የጋዛ የተኩስ አቁም ሀሳብን እንደተቀበለ እና ሃማስም በአሜሪካ የተረቀቀውን የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀበል ጥሪ አቅርቦ ነበረ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia