የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ ፓርቲ ዲሞክራቲክ አሊያንስ በአዲሱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በጥምረት ለመስራት መስማማቱን ተነግሯል።

የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ ፓርቲ ዲሞክራቲክ አሊያንስ በአዲሱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በጥምረት ለመስራት መስማማቱን ተነግሯል። የፓርቲው ቃል አቀባይ እንዳሉት የፓርቲው የፌደራል ምክር ቤት የፌዴራል መሪ ጆን ስቲንሁይሰን እና የፓርቲው ተደራዳሪ ቡድን በሃገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የጥምር መንግስት ለመመስረት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።ይህም ሕገ መንግሥስታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ፣ የሀገሪቱን ሠላም ለመረጋገጥ እና የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት ይረዳል ሲሉ ቃል አቀባዩ አክለዋል። " ዲሞክራቲክ አሊያንስ ለሁሉም የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች የተሻለ ነገን የሚያረጋግጥ የተረጋጋ መንግስት ለመመስረት በማለም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ መሥራቱን ቀጥሏል" ሲሉ ቃል አቀባዩ ሶሊ ማላቲ መናገራቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። እ.አ.አ ግንቦት 29 በደቡብ አፍሪካ የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫን ተከትሎ የአገራዊ አንድነት መንግስት እንዲቋቋም የገዢው አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ጠይቋል። ኤኤንሲ ከወዲሁ ከዲኤ ጋር ብዙ ድርድሮች አድርጓል ተብሏል። ሆኖም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሚመራው “ኡምኮንቶ ዌ ሲዝዌ” (MK) እና ጁሊየስ ማሌማ የሚመሩት “የኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮች” ፓርቲዎች፤ በተለያዩ ምክንያቶች ከዲኤ ጋር ሊተባበሩ እንደሚችሉ በመግለፅ መንግስትን ለመቀላቀል ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik