የማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ቺሊማ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው አለፈ
"የፍለጋ እና የህይወት አድን ቡድኑ የአውሮፕላኑን ስብርባሪ አግኝቷል፤ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሁሉም ተሳፋሪዎች በደረሰው አደጋ ሳቢያ ህይወታቸውን አጥተዋል፤ "ይህ ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ በቃላት ሊገልፅ አይችልም "ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ ተናግረዋል ።
ሰኞ ማለዳ፤የማላዊውን ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሎስ ቺሊማን የጫነበት አይሮፕላን ከዋና ከተማዋ ሊሎንግዌ አየር መንገድ እንደተነሳች ከራዳር መሰወሯ እና ምክትል ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍራ እንደነበር ተገልጿል።
የማላዊ ወታደራዊ ዋና አዛዥ ፖል ቫለንቲኖ ፒሪ እንዳሉት አውሮፕላኑን ለመፈለግ ሁለት መቶ ወታደሮች ተሰማርተው እንደነበር ገልጸው፤ አውሮፕላኑ የጠፋበት አካባቢ ምንም ዓይነት ነዋሪ አለመኖሩ ፤ እንዲሁም ጊዜው ጠዋት በመሆኑ የነበረው ጭጋጋማ አየር የፍለጋ ስራው ውስብስብ እንዳደረገው ጀነራሉ ተናግረዋል።
የማላዊ ጎረቤት ሀገራት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መላክን ጨምሮ በፍለጋው ላይ እገዛ ለማድረግ ፍላጐት ማሳየታቸውን ገልጸው፤ በተጨማሪም አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ እስራኤል እና ኖርዌይም እንዲሁ ለፍለጋው ድጋፍ ለማድረግ ሃሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማህመት በምክትል ፕሬዝዳንቱ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ለማላዊ ህዝብ ትልቅ ጉዳት ነው፤ የአፍሪካ ህብረት ከፕሬዝዳንት ላዛሩስ ማካርቲ ቻክዌራ መንግስትና ህዝብ ጎን ነው ማለታቸውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia