የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማጠቃለያ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች
◾ብሪክስ በጂኦፖለቲካ ውስጥ ካሉት ዋልታዎች አንዱ መስሎ አይታይም እና እራሱን ከአለም ለመነጠል አይሞክርም።
◾በጦር ሜዳ ሩሲያን ማሸነፍ የሚለውን የምዕራቡን ዓለም ስሜት በየትኛውም የብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ድጋፍ የለውም።
◾አሜሪካ እና አጋሮቿ የአለም አቀፍ የገንዘብ ሥርዓት መዋቅርን እያጣጣሉ ይገኛሉ። የዶላርን በመጠቀም የቅኝ ግዛት ስልትን እና ሌሎች የማይታወቁ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ነው።
◾ የብሪክ ሚኒስትሮች አዲስ የአለም ስርአት ለመፍጠር የማይቋረጥ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የስብሰባው ተሳታፊዎች አሳስበዋል።በዚህ ሂደት ውስጥ ብሪክስ የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበት የጋራ መገባባት አለ።
◾ብሪክስ ሀገራት የዓለም ኢኮኖሚ አቀጣጣይ እንደሚሆኑ ሁሉም ያውቃል።
◾ የብሪክስ ስብሰባ ውጤትን ተከትሎ በአለም አቀፍ አጀንዳዎች ዙሪያ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ የጋራ መግለጫ ሰኞ እለት ቀርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia